Welcome to Lideta Subcity Woreda 8 Civil Registration and Residency Service Office!       እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       Baga gara Waajjira Galmee Siivilii fi Tajaajila Jireenyaa Kutaa Magaalaa Lidetaatti Nagaan Dhuftan!

የጽ/ቤቱ ኃላፊ መልእክት

እንኳን ወደ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት በሰላም መጣችሁ። ጽሕፈት ቤታችን የወረዳችንን ነዋሪዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችና ጥቅሞች ለማስከበር ወሳኝ የሆኑትን የነዋሪነት መታወቂያ፣ የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎቶችን በቅንነት፣ በታማኝነትና በግልጽነት ለመስጠት ሌት ተቀን እየሠራ ይገኛል። ዋነኛ ዓላማችን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓታችንን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ከወረቀት ቢሮክራሲ የጸዳ በማድረግ ለእያንዳንዱ የአካባቢያችን ነዋሪ የሚገባውን ጥራት ያለውና ፈጣን ምላሽ መስጠት ነው።

የአንድ አካባቢ ሁለንተናዊ ልማትና መልካም አስተዳደር የሚረጋገጠው ትክክለኛና ወቅታዊ የነዋሪዎች መረጃ ሲኖር ነው። በመሆኑም ጽሕፈት ቤታችን የሕዝብ መረጃዎችን በአግባቡ በመያዝ፣ የተደራጀና ተዓማኒነት ያለው የመረጃ ሥርዓት በመገንባት የወረዳችንን የልማት ዕቅዶች ስኬታማ ለማድረግ የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የአሠራር ማሻሻያዎችን በመተግበር፣ የአገልግሎት ፈላጊዎችን እንግልት ለመቀነስና እርካታን ለማሳደግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን ቀጥለናል።... ተጨማሪ ያንብቡ

ወ/ሮ ሲዲሴ ባይሳ , የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ
image description

የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መነሻ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

በተጨማሪም በጽ/ቤት የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ የአገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በተቀመጠላቸው ስታንዳርድ መሰረት ፍህታዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡና ተገልጋዮች ምን ዓይነት አገልግሎት በምን ዓይነት ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ግንዛቤ በመፍጠር በዚህም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲኖር፣ በህዝብና መንግስት መካከል መተማመን እንዲፈጠር፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂት ለመፍታት በምናደርገው ጥረት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሱቡ ከጽ/ቤቱ ጎን እንዲቆሙ እናሳስባለን፡፡